Fana: At a Speed of Life!

ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ መሪዎች በመዲናዋ በቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተሰሩ ስራዎችን ጎበኙ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለመማማሪያ መርሐግብር ወደ መዲናዋ ለመጡ መሪዎች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉና ለህጻናት ምቹ እንዲሆኑ የተሰሩ ስራዎችን አስጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ ትምህርት ቤቶች የትውልድ ግንባታ ስራ መሰረት በመሆናቸው ቅድመ መደበኛ ትምህርትን ከማስፋፋት ጀምሮ 223 ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶችን፣ አምስት ትምህርት ቤቶችንና 97 ጤና ጣቢያዎችን ሞዴል በማድረግ ማሸጋገር ችለናል ብለዋል።

“ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለመማማሪያ መርሐግብር ወደ መዲናችን ለመጡ መሪዎች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉና ለህጻናት ምቹ እንዲሆኑ፣ ህጻናት በጨዋታ መልክ መማር እንዲችሉ፣ የህጻናትን ጤና ለመጠበቅ እና የተሟላ እድገት እንዲኖራቸው ትምህርት ቤቶችን እና ጤና ጣቢያዎችን ለህጻናት ምቹ ለማድረግ እና ለማሸጋገር የሰራናቸውን ስራዎች አስጎብኝተናል” ነው ያሉት።

የትውልድ ግንባታ ስራችንን ውጤታማነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማረጋገጥ እነዚህን ሞዴል ስራዎች በማስፋት በቀጣይ በልዩ ትኩረት ትምህርት ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት መስራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.