በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2ሺህ136 ደርሷል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2ሺህ136 ደርሷል።
በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 245 ሰዎች ውስጥ 190 ሰዎች ከአዲስ አበባ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።
በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 245 ሰዎች መካከል 85 ሰዎች ቦሌ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 22 ሰዎች ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 22፣ አራዳ 16 ፣ ልደታ 10 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በአጠቃላይም እስካሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 496 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው ቦሌ 375 እንዲሁም በጉለሌ ክፍለ ከተማ 256 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።