Fana: At a Speed of Life!

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ተናገሩ፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው ከቻይና ሁናን ግዛት ለመጡ የተለያዩ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል፡፡

በመድረኩ በአግሮ ፕሮሰሲንግና ማዕድን ዘርፍ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸዉ የቻይና ባለሀብቶች ጋር ኢንቨስትመንት ተኮር ዉይይት ተካሂዷል።

ኮርፖሬሽኑ ትኩረት ካደረገባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተጨማሪ በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ መሰማራት የሚፈልጉ የቻይና ኩባንያዎችን ለመቀበል ዝግጁት እንዳለ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመተግበር ባለሀብቶችን በፈጣን መንገድ ለማስተናገድ ዝግጅት መደረጉንም አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን ጠንካራ የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጡን ለማሳደግና ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በመድረኩ ምክክር መደረጉን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.