Fana: At a Speed of Life!

 ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የኢኮኖሚ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሚካይል ጃባሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በውይይቱ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ ተባብሮ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል።

አዘርባጃን በኢትዮጵያ ያለውን አስተማማኝ የመልማት ጸጋ እና ዕድሎችን በመጠቀም በተለይም ገቢ በማሳደግ፣ በኢንቨስትመንትና በስትራቴጂካዊ ስራዎች ያላትን ልምድ ለማካፈል ፈቃደኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በጋራ መልማት የሚያስችሉ ዕድሎችን ሁሉ በጋራ ለመጠቀም አዘርባጃን ቁርጠኛ መሆኗን አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.