Fana: At a Speed of Life!

የከባድ ጭነትና ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች የእውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለድንበር ተሻጋሪ የከባድ ጭነት እና ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች የእውቅና ፌስቲቫል እና ገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን እየተካሄደ ነው።

መርሐ ግብሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት፡፡

በመርሐ ግብሩ ሀገርን በቅንነት እያገለገሉ ለሚገኙ የከባድ ጭነትና ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እውቅና እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በሥራ ላይ እያሉ በትራፊክ አደጋ ጉዳት ለደሰሰባቸው፣ ሕይወታቸውን ላጡ አሽከርካሪዎች ቤተሠብ እንዲሁም ጉዳት ለደረሠባቸው ለዘርፉ አገልጋዮች የሚውል ገቢ  እንደሚሰበሰብ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ ባለሃብቶች፣ የአሽከርካሪ ማህበራት ተወካዮች እና በዘርፉ የተሠማሩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በትዕግሥት አሥማማው  እና ሰሎሞን ይታየው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.