የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ 21ኛውን የሚኒስትሮች ስብሰባውን አካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በናይሮቢ እየተካሄደ ከሚገኘው የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ጎን ለጎን 21ኛ የሚኒስትሮች ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
በመድረኩ በድንበር አካባቢ የሚገኙ መሬቶችን በተመለከተ ኢኒሼቲቩ ያፀደቃቸው ስምምነቶችን አፈፃፀም ላይ ምክክር መድረጉ ተመላክቷል፡፡
የኢኒሼቲቩን ፕሮጄክቶች ተግበራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ቀጠናዊ ባለቤትነት እና ትብብርን ማጎልበት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ በድንበር አካባቢ ባሉ ማህበረሰቦች የሚከሰቱ ልዩነቶችን ለመፍታት እና በቀጣናው ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ሃብትን ማጠናከር እና ጠንካራ አጋርነት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ ሊቀ መንበር ማሪ ሎሬ የተመራው ስብሰባው ለቀጠናዊ አንድነትና ብልፅግና ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል መባሉን ከገንዘብ ሚስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በኬንያ ናይሮቢ “የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን እና ዓለም አቀፍ የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ማሻሻያ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ መሆኑ ይታወቃል።