Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማት ሰራተኞች በመምሰል የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪደር ልማት ሰራተኞች በመምሰል ለልማት የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ኬብሎችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ፖሊስ እንደገለፀው÷ ተጠርጣሪዎቹ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ላይ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው እሪ በከንቱ እና መሀሙድ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ለኮሪደር ልማት የተዘረጉ ልዩ ልዩ ኬብሎችን በመቁረጥ እና በመስረቅ ጉዳት አድርሰዋል፡፡

በወንጀሉ ተሳትፎ ያላቸው ከ10 በላይ ተጠርጣሪዎችን በክትትል በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገለው ፖሊስ፤ ባደረገው ምርመራ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ለኮሪደር ልማት የተዘረጉ ኬብሎችን መስረቃቸውን ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ የተሰረቁትን የመሰረተ ልማት አውታሮችን ሱቅ ተከራይቶ ለሚገዛ ተቀባይ ማስረከበቸውን መረጃ የደረሰው ፖሊስ በህግ አግባብ ባደረገው ምርመራ ለኮሪደር ልማት ተብለው የተዘረጉ ኬብሎች ጨምሮ ሌሎች ለመሰረተ ልማት አገልግሎት የተዘረጉ ልዩ ልዩ ኬብሎችን በኤግዚቢትነት መያዙ ተገልጿል፡፡

የመሠረተ ልማት አውታሮች ለህብረተሰቡ ግልጋሎት እንዲሰጡ ታስቦ የሚገነቡ በመሆኑ ነዋሪው ከጉዳትና ከመሰል ስርቆት ሊጠብቃቸው እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ በመረጃው አስገንዝቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.