Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮችና ሌሎች 4 የባለድርሻ አካላት ወኪሎች በየግላቸው በመወያየት ላይ ናቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ወክለው የተመረጡ 121 የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች እና ሌሎች አራት የባለድርሻ አካላት ወኪሎች በየግላቸው በቡድን በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዛሬ ክንውንን አስመልክቶ ባወጣው መረጃ ውይይቱ ቀጥሎ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሶስቱ የመንግስት አካላት (ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና ሕግ ተርጓሚ) ተወካዮች፣ የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች በመወያየት ላይ መሆናቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.