Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሲንጋፖር እየተካሄደ በሚገኘዉ የዓለም ከተሞች ጉባኤ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አበቤ በሲንጋፖር እየተካሄደ በሚገኘዉ የዓለም ከተሞች ጉባኤ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ጉባኤው ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና አረንጓዴ በማድረግ፣ የአየር ብክለትን መከላከል እና የፈጣን ለውጥ ማዕከል በማድረግ ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራ ስለማኖር በሰፊው እየመከረ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በጉባኤው ከንቲባ አዳነች በC40 አባል ከተሞች አማካይነት በተዘጋጀዉ የፓናል ዉይይት ላይ የተሳተፉ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ቀጣይነት ያለው እድገት በማረጋገጥ ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች፣ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ልምድ አካፍለዋል፡፡

በተለይም የወንዝ ዳርቻ ስራዎች፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርኮች ግንባታ፣ የአረንጓዴ ልማት ኢንሼቲቭ፣ የኮሪደር ልማት ስራዎች እንዲሁም ሰው ተኮር ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥጠዋል፡፡

ከጉባኤው ተሳትፎ ጎን ለጎን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሲንጋፖር ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴስሞንድ ሊ፣ ከተለያዩ  ከንቲባዎች፣ ከተማ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም በከተሞች ዙሪያ ከሚሰሩ የድርጅት ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የከንቲባ ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.