Fana: At a Speed of Life!

ኬልያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን በይፋ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኬልያን ምባፔ በነፃ ዝውውር ሪያል ማድሪድን ተቀላቅሏል፡፡

ከፈረንሳዩ ክለብ ፓሪስ ሴን ዠርሜ (ፒ ኤ ሲ ጂ) ጋር ያለው ውል በፈረንጆቹ ሰኔ 30 2024 ላይ የሚያበቃው ምባፔ በአምስት ዓመት ኮንትራት ነው የአውሮፓ ሻምፒዮኖቹን የተቀላቀለው፡፡

ቀደም ሲል በቃል ደረጃ ማድሪድን እንደሚቀላቀል የገለፀው ምባፔ ከፒ ኤስ ጂ ጋር ያለው ውል በተጠናቀቀ በማግስቱ የላሊጋው የዝውውር መስኮት ሲከፈት ወደ ስፔን ያቀናል ተብሏል፡፡

ሪያል ማድሪድ የተጨዋቹን ኮንትራት በተመለከተ በቀጣይ ሳምንት መግለጫ ይሰጣል የተባለ ሲሆን ከዩሮ 2024ቱ የአውሮፓ ዋንጫ አስቀደሞ ተጫዋቹን ወደ ቤርናባኦ ለማመጣት መቀዱ ተገልጿል፡፡

የ25 ዓመቱ አጥቂ ኬልያን ምባፔ የ2018ቱን የዓለም ዋንጫ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር ዋንጫ ማንሳት የቻለ ሲሆን በፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒ ኤስ ጂ 256 ጎሎችን በማስቆጠር የክለቡ የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ መሆኑ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.