Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከኳታር ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ከኳታር ዩኒቨርሲቲ ጋር መፈራረሙን አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)÷ ስምምነቱ በኳታር እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው የላቀ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ስምምነቱ በዋናነት የኳታር ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎቱን የገለፀበት መሆኑን እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ክፍሎች ከኳታር ፋውንዴሽን ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የህክምና ትምህርት ክፍሎቹ ከኳታር ዩኒቨርሲቲ እና ከኳታር ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የህክምና እና የቀዶ ጥገና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማገዝ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ማቲዎስ ኢንሰርሙ(ዶ/ር)÷ የዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል በኳታር ጉብኝት ማድረጉን እና በተለያዩ ዘርፍች በትብብር ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ማድረጉን አስታውሰዋል።

ኳታር ፋውንዴሽን ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ዘርፍ ላይ ድጋፍ ለማድርግ የሁለት ዓመት ፕሮጀክት ቀርፆ ተግባራዊ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክ ድጋፎችን ለማድረግ እና በአጋርነት ለመስራት እንደሚፈል መግለፃቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኳታር ዩኒቨርሲቲ ልዑክ ዩኒቨርሲቲው የቴክኒክ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት አረጋግጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.