Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ህብረት ማህበር አባላት ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ህብረት ማህበር አባላት ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጀነር ታከለ ኡማ ከተለያዩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በየካ ክፍለ ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ ከ1ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል::

ኢንጀነር ታከለ በመርሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ የሆነውን ኮቪድ 19 ከመከላከል ጎን ለጎን ነዋሪዎች ባሉበት እና በሚኖሩበት አካባቢ ችግኝ ከመትከል ባለፈ ከአሁን ቀደም የተተከሉ ችግኞችን እንዲንከባከቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከሚተከሉት አገር በቀል ችግኞች በተጨማሪ ለከተማ ግብርና የሚሆኑ የፍራፍሬ ተክሎች የተዘጋጁ ሲሆን ነዋሪዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚተከለው 5 ቢሊየን ችግኞች ከ1 ቢሊየን በላይ ችግኝ በከተሞች የሚተከል ሲሆን በአዲስ አበባ 7 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.