Fana: At a Speed of Life!

በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት እና ክብር’ በሚል መሪ ሀሳብ በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

ህዝባዊ መድረኩን እየመሩት የሚገኙት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ የሰላምን ዋጋ የሚረዳ በመሆኑ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ከህዝቡ ጋር በመተባበር እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የአማራ ክልልን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ማንኛውም የህዝብ ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ የሚችለው በሰላማዊ አማራጭ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው በበኩላቸው የሚስተዋለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በተደረገው ርብርብ አንፃራዊ ሰላም መገኘቱን ጠቅሰው፤ ይህንን ሰላም ዘላቂ ማድረግ እና የልማት ሥራዎችን በአግባቡ መፈፀም ያስፈልጋልም ማለታቸውን የአማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.