የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በሐረሪ ክልል የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የአመራር አባላት በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኳይ ጆክ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የአመራር አባላት ይገኙበታል።
በክልሉ ከተማና ገጠር ወረዳዎች ምርትና ምርታማነትን ለማጎልበት የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ጨምሮ በግብርና ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ተጎብኝተዋል።
ከትንሽ ሥራ ተነስተው ውጤታማ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን የስራ እንቅስቃሴም በምልከታው ተካቷል።
የጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ የእንክብካቤ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችም እንዲሁ መጎብኘታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።