አቶ ኡሞድ ኡጁሉና ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በአፋር ክልል የልማት ስራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እና የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
የሥራ ሃላፊዎቹ የ200 ሄክታር የእንስሳት መኖ እርሻ፣ የሙዝ ክላስተር እርሻ፣ የፍራፍሬ ክላስተር እርሻ፣ የችግኝ ጣቢያ፣ እንዲሁም በማህበረሰብ የታረሰ የ530 ሄ/ር የሽንኩርት ማሳን ተመልክተዋል፡፡
በአፋር ክልል እየተሰራ ያለው የግብርና ስራ ሀገሪቱ ያቀደችውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እቅድ ትግበራ አጋዥ ነው መባሉን ከጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከተረጂነት እና ከጠባቂነት መንፈስ በመላቀቅ በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት በተግባር እያሳዩ የሚገኙ የልማት ስራዎችም መጎብኘታቸው ተገልጿል።