የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ኢትዮጵያ የተከበረው 1 ሺህ 445ኛው ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።
በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በተለይም ለሃይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ለወጣቶች ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል።
የፀጥታ ኃይሎች ከህብረተሰቡና ከበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር በመቀናጀት የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ በመወጣታቸው ግብረ-ኃይሉ ማመስገኑንም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡