የገቢ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም ለታለመለት ዓላማ ማዋል ይገባል – አቶ ደስታ ሌዳሞ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ ማዋል ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡
የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የገቢና በጀት አፈፃፀም ግምገማና የ2017 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድና የበጀት አቅጣጫ ጠቋሚ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አስተዳደር የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
አቶ ደስታ ሌዳሞ÷ የገቢ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ ማዋል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት የገቢና በጀት አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድና የበጀት አቅጣጫ ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበትም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡