በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች መሰጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በ183 ጣቢያዎች ፈተናው መሰጠት መጀመሩን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ፈተናው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተና አስፈጻሚዎችን ጨምሮ በቂ የጸጥታ አካላት መመደባቸውንም አስታውቀዋል።
ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ደረጃቸውን የሚመጥን ሞዴል ፈተና መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡