በአውሮፓ ዋንጫ ጀርመን ሁለተኛ ድሏን አስመዘገበች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አስተናጋጅ ጀርመን ዛሬ ባደረገችው ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሀንጋሪን 2 ለ 0 ረትታለች፡፡
ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የጀርመንን ጎሎች በ22ኛው ደቂቃ ሙሴላ እንዲሁም በ67ኛው ደቂቃ ጉንዶጋን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በመጀመሪያው የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ጀርመን ስኮትላንድን 5 ለ 1 ማሸነፏ ይታወሳል፡፡
የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ የዛሬ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት 4 ሠዓት ላይ ስኮትላንድ ስዊዘርላንድን ትገጥማለች፡፡
ቀን 10 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ክሮሺያ እና አልባኒያ 2 አቻ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡