አራቱ የክልል ርእሰ መስተዳድሮች በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድሮች በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸው÷ቀጣይ ሥራዎች እና የጎንዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
በዚህም በተለይ በሰላም፣ በህዝቦች የእርስ በርስ ትስስር፣ በኢኮኖሚ ግንኙነት እና በጋራ ልማት ዙሪያ መወያየታቸውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይ በአዲሱ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ወር ሌሎች አመራሮችን ያሳተፈ እና በዘላቂነት በጋራ በሚከናወኑ አጀንዳዎች ዙሪያ ለመወያየት ዕቅድ መያዙም ታውቋል።