Fana: At a Speed of Life!

የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራ ሠራዊቱ ባለበት ሁሉ ይከናወናል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሠራዊቱ በሚገኝበት ሁሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታወቁ፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመከላከያ የሎጂስቲክ ዋና መምሪያ ሥር በመልካ-ቃሊቲ አካባቢ በሚገኘው ማዕከል ችግኝ መትከላቸውን እና በሠራዊቱ ደረጃ መርሐ-ግብሩን ማስጀመራቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሐሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር  በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሠራዊቱ በሚገኝበት ሁሉ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.