የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ በአማርኛ ቋንቋ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች በፕሮግሙ ላይ ታድመዋል።
ዩኒቨርሲቲው በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠቱን አድንቆ፤ የተማሪዎቹ በአማርኛ ቋንቋ ሰልጥነው መመረቅ በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጿል።
በቀጣይም የቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጂያ ዲዦንግ የተመራ ልዑክ በመጭው ሐምሌ ወር በአዲስ አበባ ጉብኝት ያደርጋል መባሉን ከቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡