Fana: At a Speed of Life!

 አቶ አህመድ ሽዴ የዶራሌ ወደብን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በጅቡቲ የሚገኘውን የዶራሌ ባለ ብዙ ዓላማ ወደብ ጎብኝተዋል፡፡

በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት÷ የሚኒስትሩ ጉብኝት በዶራሌ ወደብ  ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን ወጪ እና ገቢ ምርቶች ፍሰትን ለመመልከት ያለመ ነው፡

በጉብኝቱ አቶ አህመድ ሽዴ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውን የአፈር ማዳበሪያ ጭነት እንቅስቃሴን መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡

የዶራሌ ባለ ብዙ ዓላማ ወደብ ከጅቡቲ ከተማ በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ የአፈር ማዳበሪያን ጨምሮ የኢትዮጵያ ወጪ እና ገቢ ምርቶች የካርጎ ጭነቶች ይደረጉበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.