Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የነበረውን የነቀምቴ ስቲል ፕሮሰሲንግ ፕላንት ፕሮጀክትን ለማስቀጠል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የጣልያኑ ዳኔሊ ኩባንያ ከለውጡ በፊት ተቋርጦ የቆየውን የነቀምቴ ስቲል ፕሮሰሲንግ ፕላንት ፕሮጀክትን ለማስቀጠል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ እና የዳኔሊ ግሩፕ የአፍሪካ አጋርነት ፕሮጀክት ፕሬዚዳንት ዳኒሎ ድሮሊኒ ናቸው፡፡

የነቀምቴ ስቲል ፕሮሰሲንግ ፕላንት ፕሮጀክት ከሀገራዊ ለውጡ በፊት 50 ሚሊየን ዩሮ ወጥቶበት ወደ ተግባር ሳይገባ የቆየ ፕሮጀክት መሆኑን የግሩፑ መረጃ አመላክቷል፡፡

ፕሮጀክቱ 300 ሺህ ቶን ብረት የማምረት አቅም ያለውና የተለያዩ ሪባርና የብረት ፕሮፋይሎችን ለማምረት ያስችላል ተብሎ መጀመሩም ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ለዓመታት ተቋርጦ የቆየውን ፕሮጀክት ወደ ስራ ለማስገባት የቴክኖሎጂው አቅራቢ ከሆነው ኩባንያ ጋር ስምምነት መፈረሙ ነው የተገለጸው፡፡

በስምምነቱ መሰረትም የኩባንያው ባለሙያዎች የኢንስፔክሽንና የማማከር ስራዎችን በማከናወን እና ተከታታይ ስራዎችን በመሥራት ፕሮጀክቱ ወደ ስራ እንዲገባ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ለሀገሪቱ የብረት ምርት አቅርቦት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረውም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.