Fana: At a Speed of Life!

‹‹ቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ተፈጥሮና የበለፀገች ሀገር ይገባዋል!

ለዚህ ደግሞ የአረንጓዴ አሻራ ዋናው የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያና የአረንጓዴ ልማት ማሳኪያ ተጨባጭ ዕርምጃችን ነው።

ዛሬ የወቅቱ የዓለማችን ወሳኝ አጀንዳ በሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ ማስተግበሪያ መርሐ ግብር ላይ ታድመናል፡፡

ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆነው የስንዴ ልማት ፕሮግራማችን በአየር ንብረት ለውጥ እየደረሰብን ያለውን ተጽዕኖ እንድንቋቋምና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ ምላሽ ለመስጠት አቅም ሆኖናል፡፡

በሌላ በኩል የታዳሽ ኢነርጂ አቅርቦት ሥራ ሀገራችንን ከኢ-ታዳሽ የኢነርጂ ምንጭ ወደ ታዳሽ ምንጭ የቀየረ ነው፡፡

በመሆኑም ሀገራችን የቀረጸቻቸውን የአየር ንብረት እና የአካባቢ ፖሊሲዎችና ዕቅዶች በአግባቡ እንዲፈጸሙ መላው የሀገራችን ህዝብ እና አጋር አካላት በአንድነት መንፈስ እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡›› – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.