Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ በተከሰተው የእሳት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ የገበያ ማዕከል ትናንት በተከሰተው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በቅንጅት ርብርብ እንዲደረግ አቶ አደም ፋራህ ጥሪ አቀረቡ፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ ገበያ ማዕከል ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ጉዳት ተመልክተዋል፡፡

አቶ አደም በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ለዚህም በድሬዳዋ አስተዳደር የተጀመረውን የመልሶ ማቋቋም ስራ ሁሉም አካል እንዲደግፍ ጥሪ ማቅረባቸውን የሐረሪ ክልል መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

አቶ ኦርዲን በበኩላቸው የድሬዳዋ አስተዳደር በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት የሐረሪ ክልል መንግስት እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.