1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 178 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከሚያዝያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ ሥራ ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱ ዜጎች ቁጥር ከ55 ሺህ በላይ መሻገሩ ተገልጿል፡፡