የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ በሽብርተኛው ሸኔ ታግተው የነበሩ ተማሪዎች ተለቀዋል አለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ሸኔ ቡድን ባለፈው ሣምንት ታግተው የነበሩ ተማሪዎች መንግሥት ባደረገው ጥብቅ ኦፕሬሽን አብዛኞቹ መለቀቃቸውን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
ባለፈው ሣምንት ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ከነበሩት “167 ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ መለቀቃቸውን” የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ አረጋግጠዋል።
ተማሪዎቹ ከታገቱበት የተለቀቁት የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት ርምጃ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹ የታገቱት በአሸባሪው የሸኔ ቡድን መሆኑን ገልጸው፤ ቀሪዎቹን ተማሪዎች ከታገቱበት ለማስለቀቅ የፀጥታ ኃይሎች ጥረት እያደረጉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡