Fana: At a Speed of Life!

የጎርጎራ ፕሮጀክት ታሪክ፣ ተፈጥሮና የሰው ልጅ ሐሳብ የተስማሙበት ሥራ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎርጎራ ፕሮጀክት ታሪክ፣ ተፈጥሮና የሰው ልጅ ሐሳብ የተስማሙበት ድንቅ ስራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ግንባታ ተጠናቅቆ ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቋል፡፡

አምባሳደር ታዬም ይህን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ የጎርጎራ ፕሮጀክት ታሪክና ተፈጥሮ በጉልህ የሚመሰክሩለት ድንቅ ስፍራ መሆኑን ተናግረዋል።

ታሪክን አስቦ ከዛሬ ጋር በማስተሳሰር ውብ አድርጎ መስራትና ለቱሪስት መስህብ ማድረግ ይቻላል ብለው ያሳዩ የሐሳብና የተግባር ባለቤቶችን ማድነቅ ይገባል ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ይህ ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ዕውን እንዲሆን ላደረጉት የላቀ አስተዋጽኦ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት፡፡

የጎርጎራ ፕሮጀክት ታሪክ፣ ተፈጥሮና የሰው ልጅ ሐሳብ የተስማሙበት ዘመን ተሻጋሪ ድንቅ ሥራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ እንደዚህ አይነት ግዙፍ ሐሳብ አስቦ በተግባር መግለጥ ትልቅ እመርታ መሆኑንም ተናግረዋል።

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ዋነኛ የቱሪት ማዕከል የሚሆን ድንቅ ስፍራ መሆኑን ጠቅሰው የውጭና የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች እንዲጎበኙት ጋብዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.