Fana: At a Speed of Life!

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዐሕመድ (ዶ/ር) ትናንት ተመርቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉዳዩን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ÷ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ተስፋ የሰነቀ ዘመን ተሻጋሪ የሀገር ሃብት መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እምቅና አስደናቂ የቱሪዝም ሃብቶች ቢኖሩም በመሰረተ ልማት እጥረት ለጎብኝዎች እምብዛም ተደራሽ ሳይሆኑ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በስፋትና በጥራት እየለሙ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

መንግሥት ለቱሪዝም ልማት በሰጠው ትኩረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ አመንጭነት ዜጎችን በማስተባበር በርካታ ፕሮጀክቶች ተገንብተው እየተጠናቀቁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ የጎርጎራና አካባቢው አስደናቂ ስፍራ ለዘመናት ልማት እርቆት ውበቱና ሃብቱ ሳይገለጥ መቆየቱን ገልጸው አሁን ላይ ለቱሪስቶች ምቹ መዝናኛ ሆኖ መሰራቱን አስረድተዋል፡፡

በታካዊው ስፍራ ላይ በዘመናዊ መልኩ የተገነባው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ሁነኛ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን ዝግጁ ሆኗል ብለዋል።

በአማራ ክልል የተለያዩ መሰረተ ልማቶች፣ የቱሪዝም ልማትና ኢንዱስትሪዎች እየተስፋፉ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.