አቶ አገኘሁ ተሻገር በአርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አከናውነዋል ።
አፈ ጉባኤው በዚህ ወቅት ÷ በሀገሪቱ ባላለፉት አመታት በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐግብር ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ገልጸው ይህም የደን ሽፋንን ከፍ ለማድረግና ለታቀደው የአረንጓዴ ልማት ግብ መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባዉዲ ÷ በክልሉ በሁሉም ዞኖች አንድ ተራራ የማልማት ተግባር በህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ በበኩላቸው÷ በክልሉ በሚተገበረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የችግኞችን የፅድቀት መጠን ወደ 90 በመቶ ለማሳደግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡