Fana: At a Speed of Life!

መርሐ-ግብሩ ሀገር በቀል እጽዋትን መሰረት ያደረገ ሥራ ለማከናወን እድል መፍጠሩ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሀገር በቀል እጽዋቶችን መሰረት ያደረገ የአካባቢ ጥበቃ ስራ ለማከናወን ምቹ እድል መፍጠሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን በጫካ ፕሮጀክት ሀገር በቀል የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞችን ተክለዋል።

በመርሐ-ግብሩም በባህር ዛፍ ተክል የተሸፈኑ ስፍራዎችን በሀገር በቀል እጽዋቶች የመተካት ስራ መከናወኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚሁ ወቅት ሚኒስትሯ እንዳሉት÷ የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ለሁለተኛ ጊዜ የሀገር በቀል ችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች ከዚህ ቀደም በሀገር በቀል የእርከን ጥበብ በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ የፍራፍሬ ችግኞች መትከላቸውን አስታውሰው÷ ዛሬ ደግሞ ቀደም ብለው በባህር ዛፍ ተሸፍነው በነበሩ ቦታዎች ላይ የሀገር በቀል ችግኞች መትከላቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የሀገር በቀል እጽዋቶችን መሰረት ያደረገ የአካባቢ ጥበቃ ስራ ለማከናወን ምቹ እድል መፍጠሩንም አስረድተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳትፎ በማድረግ ውጤታማ ስራ ማከናወናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ይህ የጋራ ትብብር ዘንድሮም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.