Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት የዩኒዶ ተወካይና የቀጣናው ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የስራ ጊዜያቸውን ካጠናቀቁት የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ተወካይና የቀጣናው ዳይሬክተር ሆነው ካገለገሉት ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ የነበሩት ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ በነበራቸው የስራ ጊዜ ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ልማትን በመደገፍ ላሳዩት ቁርጠኛ አመራርነት አመስግነዋል፡፡

“በቀጣይም በከተማ አስተዳዳሩ በሴቶች ክህሎት ማበልፀጊያ እና የስራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የጀመርናቸውን ተግባራት በአጋርነት መስራትን ለማስቀጠል ከስምምነት ላይ ደርሰናል” ብለዋል ከንቲባ አዳነች፡፡

በራሳቸውና በከተማ አስተዳዳሩ ስም ቀጣይ የሥራ ዘመናቸው የተቃና እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.