Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጥላሁን በዓለም አቀፍ የወጣቶች ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኮሪያ ቡሳን እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ፎረም ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

ከ30 በላይ ሀገራት የተሳተፉበት ፎረሙ በቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት፣ በሰው ሃይል ልማት እንዲሁም በትምህርትና ሥልጠና ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡

አቶ ጥላሁን በቆይታቸው ወጣቱን በዕውቀትና ክህሎት በማነጽ ውጤታማ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በባህል፣ቱሪዝምና ትምህርት መስኮች ቀጣይ የድጋፍና ትብብር ማዕቀፎች ዙሪያ እንደሚወያዩም የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.