Fana: At a Speed of Life!

ለአየር ንብርት ለውጥ የማይበገር የቡና ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው-ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ለአየር ንብርት ለውጥ የማይበገር የቡና ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ሚኒስትሩ ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ)ፕሮጀክት ፋይናስ ኦፊሰር ዳፊና ዲሎቫ ጋር የማይበገር ቡና ልማት ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአርንጓዴ ልማትን ለመገንባት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እያካሄደች መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተመድ  የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ፕሮጀክት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የቡና ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

የማይበገር የቡና ልማት ፕሮጀክትን ለማሳካት በምስራቅ አፍሪካ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ከማምረት በተጨማሪ ተወዳዳሪነትን መጨመርና የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ፋይናንስ ኦፊሰር ዳፊና ዲሎቫ በበኩላቸው ÷ፕሮጀክቱ ለአየር ንብርት ለውጥ የማይበገር የቡና ልማት ላይ የሚያተኩር መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በቡና እሴት ሰንሰለት፣ በጥራት ማሻሻልና የገበያ መዳረሻ በሚጨምርበት እና አርሶ አደሮችን በክላስተር አደራጅቶ ማሰራት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ እና ማላዊ እየተተገበረ እንደሚገኝም መግለፃቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.