Fana: At a Speed of Life!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበብ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ጀምሯል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኃላፊ ዶክተር የሺጌታ ገላው እንዳሉት ሆስቲታሉ በቀን 96 ናሙናዎችን መርመር የሚያስችል ነው፡፡

በሆስፒታሉ አንድ የመመርመሪያ ማሽን እንዳለና ወደፊት ተጨማሪ ለማምጣት እንቅስቃሴ እንደተጀመረም አስታውቀዋል፡፡

በአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክተር ማንአምኖት አገኝ በበኩላቸው የጥበበ ግዮን ስፔሻላዝድ ሆስፒታል የክልሉን የምርመራ አቅም ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

ምርመራ መጀመሩን ተከትሎ በክልሉ ስድስተኛው የናሙና መመርመሪያ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ወልዲያ ላይ ምርመራ በቅርብ የሚጀመር ሲሆን በቅርቡ በክልሉ በቀን እስከ 1 ሺህ 500 ናሙናዎችን ለመርመር እየተሠራ ነው፡፡

እዲሁም መተማ ላይ ምርመራ ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅሰው ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ማመላከታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.