ባንኩ በጎፋ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የገንዘብ ድጋፉ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሠራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ባንክ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ባሳለፍነው ሰኞ በተከሰተ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡