በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 988 ደረሰ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 988 መድረሱን የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 116 ሰዎች ውስጥ 101 ሰዎች ከአዲስ አበባ መሆናቸው ተገልጿል።
ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።
በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 101 ሰዎች መካከል 28 ሰዎች ልደታ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 21 ሰዎች ጉለሌ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ ተብሏል።
በተጨማሪም ንፋስ ስልክ ላፍቶ 14፣ ኮልፌ ቀራኒዮ 7፤ ቂርቆስ 6 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በተጨማሪም ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 17፣ አቃቂ ቃሊቲ 1፣ የካ ክፍለ ከተማ 2፣ ቦሌ 3፣ ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።
በአጠቃላይም እስካሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 683 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው ቦሌ ክፍለ ከተማ 440 እንዲሁም በጉለሌ ክፍለ ከተማ 329 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በተያያዘም ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ 2 በህክምና ማዕከል ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ አንድ በጤና ተቋም የነበረ እና አንድ በአስክሬን ምርመራ ቫይረሱ እንዳለበት የተረጋጠ ሰው ህይወት ማለፉንም ቢሮው አስታውቋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በትናንትናው እለት 88 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና በሽታ አገግመዋል ነው ያለው።