Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ የባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ልየታ መድረክና ለሀገራዊ ምክክሩ ጉባኤ ተወካዮች ምርጫ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚከናወን ተገለፀ፡፡

በሂደቱ በክልሉ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ወኪሎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት፣ የተለያዩ ማህበራትና ተቋማት እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የታዋቂ ግለሰቦች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በመድረኩ የባለድርሻ አካላት ትውውቅ በማድረግ በጋራ በመሆኑ በአጀንዳዎቻቸው ላይ እንደሚወያዩ ከምክክር ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሶስት ቀናት የውይይት ቆይታቸው የክልሉን አጀንዳዎች በመለየት በመጪው ማክሰኞ ሐምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የተጠቃለለ አጀንዳ ለኮሚሽኑ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.