Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጎብኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ስልጠና ተጠናቅቋል።

ስልጠናው እንደ ፓርቲ የብሔራዊነት ትርክትን ለመገንባት ለህዝብ ግንኙነት ሥራ አቅም የሚፈጥሩ ተሞክሮዎች የቀረቡበት መድረክ ሆኖ መጠናቀቁ ተጠቁሟል፡፡

በስልጠናው ሲሳተፉ የነበሩ ሰልጣኞችም በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተሠሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

ፓርቲው ለሕዝብ የገባው ቃል በፍጥነትና በጥራት በተግባር የተገለጠ ሆኖ መታየቱ እሳቤዎቹ በተግባር የተፈሹ መሆናቸውን ከማሳየቱ በላይ የተገኙ ውጤቶች ልማታዊ አቋሞቹን በሕዝብ ዘንድ ለማስረጽ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውን ጎብኚዎች ተናግረዋል፡፡

አመራሩና ህብረተሰቡ ከላይ እስከ ታች ድረስ በተናበበ መልኩ ያስመዘገቡት ውጤት መሆኑን የገለጹት ተሳታፊዎቹ ÷የታዩ ውጤቶችን በሁሉም ዘርፎች መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ብልጽግና ለሀገራዊ ልዕልና የሚተጋውን ያህል ሰውን ማዕከል ያደረገ የማህበረሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያካተተ ልማት ላይ ማተኮሩን በተግባር ማረጋገጥ የተቻለበት እንደሆነ መጠቆማቸውንም የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.