Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ በ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በመቐለ ከተማ በ2 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነቡ ያሉና ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።

ጉብኝቱ ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት የበቁና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን እንደሚያካትትም ተገልጿል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚጎበኟቸው መሰረተ ልማቶች መካከል በመቐለ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ 25 ቀበሌዎችን የሚያስተሳስር የጠጠር መንገድ ግንባታ እንደሚገኝበት በጊዜያዊ አስተዳደሩ የመቐለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካሕሳይ ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ የተሰሩ የተሽከርካሪና የሰው መሻገሪያ ድልድዮችም የጉብኝቱ አካል መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በርካታ የሥራ እድል የፈጠረባቸው 10 የዳቦ ማምረቻ ሼዶችም እንደሚጎበኙ ተገልጿል።

ከ60 ዓመት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የመቐለ ሆስፒታል ጥገናና የማስፋፊያ ግንባታ ሂደትን ጨምሮ ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም የጉብኝቱ መርሐ ግብር አካል መሆናቸው ተጠቁሟል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.