Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል የተደረገው የብድር ስምምነት ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ስብሰባው በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የልማት ማህበር መካከል የተደረገውን የብድር ስምምነት አዋጅ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን÷ የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጁ ላይም መክሯል፡፡
ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በብድር የተገኘው 500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመራቸውን የሪፎርም ስራዎች ለመደገፍ ያስችላል ተብሏል፡፡
በዚህም ከምክር ቤቱ የብድር ስምምነቱን አስመልክቶ ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቶ የቀረበው አዋጅ 1345/2016 ሆኖ በአንድ ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.