Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በጋምቤላ ከተማ የአረጋውያን ቤት እድሳት ፕሮግራም አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋምቤላ ከተማ የአረጋውያን ቤት እድሳት ፕሮግራም አስጀምረዋል፡፡

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ በጋምቤላ ከተማ የአምስት አቅመ ደካማ አረጋዊያን ቤቶችን የማደስ ሂደት የተጀመረ ሲሆን ቤቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀዉ ለአረጋዊያኑ እንደሚተላለፉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ የሥራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ከጋምቤላ ክልል አመራሮች እና ወጣቶች ጋር በመሆን  የጽዳትና የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂደዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋዬ ዳባ፣ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ቴንኩዌይ ጆክን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙነኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.