Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በሆሳዕና ከተማ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን አከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ የችግኝ ተከላ እና የቤት እድሳት መርሐ ግብር አከናወኑ፡፡

በመርሐ ግብሩ ከችግኝ ተከላ እና ቤት እድሳት በተጨማሪ ለ200 አቅመ ደካማ ቤተሰቦች ዱቄትና የምግብ ዘይት እንዲሁም ለ220 ተማሪዎች መማሪያ ቁሳቁስ ተበርክቷል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰን÷ የበጎ አድራጎት ስራ ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልጸው፤ ተቋማቸው በሆሳዕና ከተማ ያከናወነው የበጎነት ባህሉ የተግባር ማሳያ ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ የሚያደርጉትን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው÷ በቀጣይ በሆሳዕና ከተማ ሁለት መዋዕለ ህጻናት ግንባታ እንደሚያከናውኑ ጠቁመዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ መሃመድ ኑርዬ (ዶ/ር) በበኩላቸ ÷ በክልሉ በተለያየ ደረጃ የክረምት በጎ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ላከናወኑት የበጎ አድራጎት ስራ ምስጋና ማቅረባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.