Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በትጋት እንዲወጡ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በትጋት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በቅርቡ የተሾሙት 24ቱ አዲስ አምባሳደሮች ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ፊት ቀርበው ፥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ እና በትጋት ለመሥራት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።

ፕሬዚዳንቷ ቃለ መሐላ ለፈጸሙትን አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ባስተላለፉት መልእክት ÷ ሀገርን መወከል ትልቅ ክብር መሆኑን በመግለፅ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት አምባሳደሮቹ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በትጋት እንደሚወጡ እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በበኩላቸው ÷ ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ሀገርን ማገልገል ታላቅ ክብር መሆኑን እንደገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደሮቹ ካላቸው ልምድና ዕውቀት በተጨማሪ ሥልጠና እንደወሰዱም በመግለፅ በቀጣይ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መድረኮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በትጋት እንደምትሰሩ እተማመናለሁ ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.