Fana: At a Speed of Life!

ገቢን ማሳደግ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አንኳር ጉዳይ በመሆኑ ኢኮኖሚው በሚያመነጨው ልክ ገቢ መሰብሰብ አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አንኳር ጉዳይ በመሆኑ ኢኮኖሚው በሚያመነጨው ልክ ገቢ መሰብሰብ እንደሚያስፈልግ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ተናገሩ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ከከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

አቶ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት÷ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤታማ የሚሆነው ምርታማነትንና የገቢ አቅምን ማሳደግ ሲቻል ነው።

በመሆኑም ገቢን ዘመናዊ በሆነ የአሰራር ስርአት በተገቢው መንገድ መሰብሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሀገር ውስጥ ገቢ ከተመረተው አጠቃላይ የሀገር ውስጥ የምርት እድገት አንጻር የሚኖረውን ድርሻ ማሳደግ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አንኳር ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል።

የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ዘመናዊ የምጣኔ ሀብትና የንግድ ስርአት እንዲኖር ያግዛልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለዚህም የከፍተኛ ግብር ከፍዮች ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸው፤ ግብርን በአግባቡ በማሳወቅና በመክፈል ለሀገር እድገትና ለኢኮኖሚ ማሻሻያው መሳካት በጋራ መረባረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.