የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የአስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2016 ዓ.ም የአፈፃፀም ሪፖርትን እያቀረቡ ይገኛሉ።
በጉባዔው በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተገምግሞ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተጠቁሟል፡፡
ዛሬ እና ነገ በሚካሄደው ጉባዔ የ2017 በጀት ዓመት በጀት የሚጸድቅ ሲሆን÷የተለያዩ ሹመቶች እንደሚሰጡም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡