Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ሃጂ ኢሴ አደም÷የብልጽግና ፓርቲ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በትብብርና ውይይት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት አንዳለው አንስተዋል፡፡

በዚህም ፓርቲው በጋራ በመምከር እና በመወያየት ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ በጽኑ ያምናል ብለዋል።

ም/ቤቱ ተመስርቶ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በየጊዜው በመወያየት ችግሮችን እየፈታ መሄዱ ዴሞክራሲ እየተተገበረ ያለበት ምዕራፍ ላይ የመገኘታችን ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ በሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣ ሰላም፣ ልማት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ በፊት ስለ ነበሩ የጋራ አፈጻጸም ክፍተቶች በመወያየት እና በቀጣይ ክፍተቶችን በማረም የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ ከመግባባት ላይ መደረሱም ተጠቁሟል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.