Fana: At a Speed of Life!

ከ 7 ሺህ በላይ ሕገ- ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ዋጋ በመጨመር እና ምርት በመደበቅ ተግባር ላይ የተገኙ ከ7 ሺህ በላይ ነጋዴዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)÷ በውጪ ምንዛሪ ላይ የተደረገውን ለውጥ ምክንያት በማድረግ የተስተዋለውን የምርቶች ዋጋ መጨመር ለመግታት ከላይ እስከ ታች በተደራጀ አግባብ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መሰራቱን ነው የጠቀሱት፡፡

የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት መሰረታዊ ሸቀጦችን የጫኑ 1 ሺህ 649 ተሽከርካሪዎች ወደ ገበያ እየገቡ ሲሆን÷ከ115 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በስርጭት ሒደታ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የምርት እጥረት አለመኖሩን ገልጸው÷ከሕገ ወጥ ተግባራቸው በማይቆጠቡ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስገንዘባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ማሻሻያውን ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ምርት በመደበቅ ተግባር ላይ የተገኙ ከ7 ሺህ በላይ ነጋዴዎች አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.