በመቐለ በ2 ቢሊየን ብር ወጪ የኮሪደር ልማት ሥራ እንደሚከናወን ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቐለ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም በ2 ቢሊየን ብር በከተማዋ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ በተገኙበት በመቐለ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የማስተዋወቂያና የመገምገሚያ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካሕሳይ እንደገለፁት÷ የኮሪደር ልማት ሥራው 35 ሺህ ካሬ ሜትር በሚሸፍን ቦታ ላይ ይከናወናል።
የኮሪደር ልማቱ ዋና ዓላማ የመቐለ ከተማን ውብና ፅዱ በማድረግ ለቱሪስት መስህብ፣ ለወጣቶችና አረጋውያን ምቹ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችለውን ልምድ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መቅሰሙንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡